Easter 2023 Tour to Jerusalem
በአይነቱ ታሪካዊ የሆነ የኢየሩሳሌም ጉዞ ለፋሲካ የተዘጋጀ። ይህ ጉዞ በራሳችን ገዳም በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረበ ከመሆኑም በላይ በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ለገዳማችን የበኩልዎን ያደርጋሉ። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ማለት ነው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያን በዳግማዊቷ ዋልድባ ገዳም በካሊፎርኒያ የተዘጋጀ የፋሲካ የበረከት ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም።
ይህ የበረከት ጉዞ በብፁዕ ዶ/ር አቡነ ቴዎፍሎስ የሚመራ ይሆናል።
ለማንኛውም ተጨማሪ ጥያቄዎችና የምዝገባ ወይም የክፍያ ችግሮች ካጋጠምዎት በሚቀጥለው አድራሻ ያነጋግሩን፥
ካሊፎርኒያ : +1 (323) 206-2572
ለሰሜን አሜሪካ - +1 (703)416-9494
ለአውሮፓ - +972 549 21 20 30 (whatsApp)
Double Occupancy
Flight departing from LA, Washington DC, Toronto, Addis Ababa and Europe - መነሻ ከሎስ አንጀለስ ፣ ከዋሽንግተን ዲሲ እና ከቶሮንቶ - Contact us for domestic flights.
'ከነፃ የግብይት ቀን' ምሳ በስተቀር
ጉብኝት በዘመናዊ አውቶቡስ
Site Entrance Fee
ለአስጎብኚ እና ለአውቶቡስ ሾፌር የሚሰጡ ቲፖች
ከአየር ማረፊያ ትራንስፖርት በግላቸው ለሚመጡ
Insurance Coverage for Covid-19 -ኮቪድን የሚያጠቃልል
የእስራኤል የመግቢያ ቪዛ ለሚያስፈልጋቸው ብቻ
በዚህ ዕለት ጕዞ ወደ ቅድስት ሀገር የሚደረግበት ቀን ይሆንናል።
በዚህ ዕለት ቤንጎርዮን የእስራኤል አየር ማረፊያ ያርፋሉ፤ በዚያም የአስጎብኚዎ ድርጅት የሥራ ባልደረቦች ልባዊና መልካም የሆነ አቀባበል ያደርጉለዎታል። በቀጥታም ወደ ያዝንለዎት ሆቴል እንወስደዎትና የእረፍት ጊዜ ያደርጋሉ። ራትና አዳራችን በተያዘልዎት ሆቴል ይሆናል። የመንገዱን ድካምዎን በምቹው የሆተል መኝታ አሳርፈው በማግስቱ ኢየሱስ ክርስቶስ እግሮቹ በተመላለሱበት ምድር እርሰዎም ለመራመድ ይዘጋጃሉ።
ከቍርስ በኋላ ቅዱስ ቦታ በሆነው በደብረ ጽዮን (2ሳሙ15፣30 ማር 11፣1 ሐዋ 1፣12) ጕብኝታችንን እንጀምራለን። በመቀጠል ጌታ የደቀ መዛሙርቱን እግር ወዳጠበበትና ከነርሱም ጋር የመጨረሻዋን የፋሲካን ራት ወደበሉበት ደርብ/ቤት እናቀናለን(ዮሐ13፡4)፤ ከዚያም ወደ ንጉሥ ዳዊት የመቃብር ሥፍራና ቅድስት ድንግል ማርያም ወዳረፈችበት ወደ ዶርሚሽን ቤተክርስቲያን እንቀጥላለን። በጽዮን በር በኩል ወደ ጥንታዊቷ የኢየሩሳሌም ከተማ እንገባና የአይሁድ ብቸኛ ቅዱስ ቦታ፣ ለሙስሊሞች ደግሞ ሦስተኛው ቅዱስ ቦታ የሆነውን ምዕራባዊውን የቤተ መቅደስ ክፍል እንጎበኛለን፤ ከዚህ ሁሉ በኋላ የጸሎተ ሐሙስ ሥርዐትን ለመካፈል ወደ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንሄዳለን። ራትና አዳራችን በኢየሩሳሌም ይሆናል።
በዚህ ዕለት ኢየሱስ ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ ባልጋ ቍራኛ ተይዞ የነበረውን ሰው የፈወሰባትንና የመጠመቂያ ሥፍራ የነበረባትን ቤተ ሳይዳን/ቤተ ስዳ/ በመጎብኝት እንጀምራለን (ዮሐ 5፣ 2-9)። ከዚያም ቪያ ዶሎሮሳ የተባለውንና ኢየሱስ ካባድና ፅኑ ጸዋትወ መከራ ያለፈበትን ባለ 14 ጣቢያ መንገድ ከጲላጦስ የፍርድ አዳራሽ እንጀምርና ዳር'ዔል ሡልጣን ላይ ጕዞአችንን እናብቃለን። የአርብ ስቅለት ሥርዐትን እንካፈልና ራትና ኣዳራችን በኢየሩሳሌም ይሆናል።
በዚህ ዕለት ማለዳ ኢየሱስ በተሰቀለበት ቦታ በጎልጎታ የሚካሄደውን ሥርዐተ ቅዳሴን እንሳተፋለን። ከቍርስ በኋላ፣ በቀጥታ በመኪና ወደ ደብረ ዘይት ተራራ እንጓዛለን። እዚያ እንደደረስንም አስቀድመን ኢየሱስ ያረገበትን ሥፍራ - የዕርገት ቤተክርስቲያንን እንጎበኛለን። በመቀጠልም በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ለመግባት ወደ ጀመረባት ቦታ ወደ ቤተ ፋጌ እንሄዳለን(ሉቃ 19፣ 28-40)። ከዚያም ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ "አባታችን ሆይ" የሚለውን ጸሎት ያስተማረበትን ቦታ ፓተር ኖስተር ቤተክርስቲያን (ኢልዮና)ን እንጎበኛለን። ደብረ ዘይት ተራራ አናት ላይ ሆነን ከርቀት የጥንታዊቷን የኢየሩሳሌም ውብ መልክዐ-ምድራዊ ገጽታን እየተመለከትንም ደስ እንሰኛለን፣ ከደብረ ዘይት ተራራ ቍልቍል እንወርድና ጌታ ኢይሩሳሌምን ዐይቶ ወዳለቀሰላት(ሉቃ 19፡ 41-44) ወደ ዶሚንዮስ ፍለቨት የጸሎት ቦታ እናመራለን። ኢየሱስ ሲጸልይ ወደ ተያዘባት ወደ ጌቴሴማኒ ያትክልት ስፍራ(ማቴ 26፣ 36-58/ ሉቃ 26፡ 36-58) ወደ ታዋቂው የሕዝቦች ሁሉ ቤተክርስቲያን ጉዞኣችን እንቀጥላለን። የዕለቱ ጉዞአችን የቅድስት ድንግል ማርያምን መካነ መቃብር በመመልከት ያበቃል። ከምሳ በኋላ በሆቴላችን እረፍት የምናደርግበት ጊዜ ይኖረናል። አመሻሹ ላይ ሻማ የማብራት ሥነ-ሥርዐትና የትንሣኤ የዋዜማ ምሽት ወደ ሚካሄድበት ወደ ዳር'ዔል ሡልጣን እንሄዳለን። ሌሊት ወደ 9፡00 ሰዓት ገደማ ወደ ማረፊያ ሆቴላችን እንመለሳለን።
በዚህች ዕለት የትንሣኤ ክብረ በዓል በሐሴት፣ በደስታ ብሎም ግሩም ከሆነ የፋሲካ ምሳ ጋር እናሳልፋለን። ኣዳር በኢየሩሳሌም ከተማ ይሆናል።
ቀኑን አስገራሚ መልክዐ-ምድራዊ አቀማመጥና ገጽታ ያለውን የይሁዳ ምድረ በዳን እየተመለከትን ዜኬዎስ የወጣበትን የሾላ ዛፍና የኤልያስን ምንጭ ወደ ምንመለከትበት ወደ ኢያሪኮ በመጓዝ እንጀምራለን። ኢየሱስ በሰይጣን ወደ ተፈተነበት ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ እንወጣለን። ከዚያም ኢየሰስ በዮሐንስ እጅ የተጠመቀበትን ልዩ የዮርዳኖስ ወንዝ ቦታ፣ ካሰር አል-ያሁድ እንጎበኛል። በደቡባዊው የሙት ባሕር ዳርቻ ወደ ምትገኘው፣ በዓለምም ካባሕር ጠለል በታች 400 ሜትር የመጨረሻው ረባዳ ቦታ ወደ ሆነው ወደ ዔይን ቦኬክ እንጓዛለን። በዚያም ደረጃውን በጠበቀ ባለ4 ኮከብ ሆቴል ውስጥ በዓለም እጅጉን በታወቀውና በጨው ማዕድን በበለጸገው ውሃ ወስጥ እንዝናናለን። ስፓ፣ ጃኩዚ፣ የመዋኛ ገንዳና በዚያ በሚገኙት የመዝናኛ አገልግሎት መስጫዎች ሆሉ እየተዝናናን ደስ እንሰኛለን።
የዕለቱን ጕዟችንን በታችኛው የገሊላ ክፍል በኩል በማድረግ የኢይዝራዔልን ሸለቆንና ብሎም እንደ ዮሐንስ ራዕይ መሠረት የሰውልጆች የመጨረሻው ጦርነት የሚደረግበትን የሚግዶን አስደሳች መልክዐ-ምድራዊ ገጽታን እየተመለከትንና ደስ እየተሰኘን በቀጥታ ጌታ ብርሃነ-መለኮቱን ወደ ገልጠበት ወደ ደብረ ታቦር እናመራለን። ኢየሱስ በሰረግ ቤት ታድሞ የወይን ጠጅ ባለቀባቸው ጊዜ የመጀመሪያውን ተአምራት ያደረገበትን(ዮሐ 2፡1-11)ቃና-ዘገሊላንና በዚያም የሚገኘውን ቤተክርስቲያን እንጎበኛለን። በመቀጠልም ወደ ናዝሬት በማምራት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ደስ ይበልሽ በማለት የኢየሱስን መወለድ ለድንግል ማርያምን ያበሠረበትን(ሉቃ 1፡26-38) ጥንታዊውን የብሥራት ዋሻን እንጎበኛለን። የዮሴፍን ቤትን እንመለከትና ወደ ማሪያም ምንጭ እንሄዳለን። አዳር በጥብርያዶስ ይሆናል።
ከቍርስ በኋላ ጉዞአችንን ወደ ስብከቱ ተራራ እናደርጋለን። ከዚያም ጌታችን የተራራውን ስብከት (አንቀጸ ብጹዓን) የሰበከበትን ተራራ እንጎበኛለን(ማቴ 5፡7)። በመቀጠልም ኢየሱስ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሳ አበርክቶ ለሕዝቡ ወደ መገበበት ቦታ(ማቴ 14፡14-43) ወደ ታብጋ እንሄድና የ4ኛው ክ/ዘመን የሞዛይክ ጣራ ያለውን ቸርች ኦፍ መልቲፕልኬሽን /የበርክቶ ቤተክርስቲያን/ን እንጎበኛለን። በመቀጠልም ናዝሬትን ትቶ በመምጣት መኖሪያው ያደረገባትንና በምድር ላይም አገልግሎቱን ወደ ጀመረባት በዘልማድም የኢየሱስ ከተማ እየተባለች ወደ ምትጠራው ወደ ቅፍርናሆም እናልፋለን። በዚያም በሁለተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ምኲራብንና የቅዱስ ጴጥሮስ መኖሪያ የነበረውን ቤት እንጎበኛለን። በምሳ ሰዓት ግሩም የሆነውን የቅዱስ ጴጥሮስን ዓሣ እንመገብና በጀልባ ላይ ተሳፍርን ኢየሱስ በእግሩ የተራመደበትን የገሊላን ባሕርን እንሻገራለን(ማቴ14፡22-23)። በዘመነ ኢየሱስ የነበረውን የዓሣ አጥማጅ ጀልባ፣ "የኢየሱስ ጀልባን በኪቡጽ ጊኖሣር እንጎበኛለን። ለራትና ለአዳር ወደ ሆቴላችን እንመለሳለን።
በዚህ ዕለት የቀርሜሎስ ተራራ የእግዚአብሔር የወይን ተክልንና የታላቁ ነቢይ የኤልያስን ባዕት/ዋሻ በመጎብኘት እንጀምራለን። ከዚያም በሐይፋ የሚገኝውንና ከፍ ካለው መልክዐ-ምድራዊ ገጽታ ላይ የተንጣለለውን፣ ባትክልትም የተዋበውን የባሂኢን ያምልኮ ሥፍራ ተመልክተን ወደ ቴል አቪቭ በሚወስደው በሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ መንገድ ኣድርገን ወደ ጃፋ እናመራለን። በዚያም ነቢዩ ዮናስ ከእግዚአብሔርና ከትእዛዙ ለመኮብለል መርከብ የተሳፈረበትን ቦታና(ዮና 1፡3) ብሎም ደግሞ ሐዋሪያው ቅዱስ ጴጥሮስ በስድስት ሰዓት ያህል ይጸልይ ዘንድ ወደ ጣራው የወጣበትን የቍርበት ፋቂው የስምዖን ቤት(ሐዋ 10፡9-19) ፣ጥንታዊቷንም የጃፋን ወደብ እንጎበኛለን። በመቀጠልም ከምሳ በሗላ ጉዞአችንን ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ቤተልሔም ይሆንና፣ በባሲልካ ኔቲቪቲ ምልክት የተደረገበትን የኢየሱስን የልደት ቦታ እንጎበኛለን(ሉቃ 2፣ 1-7)። መልአከ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ብሎ ለእረኞች የጌታን ልደት ያበሠረበትን፣ መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩበትን ሥፍራ(የወተት ዋሻ)ን እንመለከታለን( ሉቃ2፡8-18)። ከሰዓት በኋላ የመጥምቁ ዮሐንስን የልደት ቦታ ዔይን ካሬምን እንጎብኛለን። ማርያም ዘመዷን ኤልሳቤጥን ለመጎብኝት የሄደችበት ሀገርና ከእርሷም ጋር የተገናኘበትን ሥፍራ ላይ ያልውን ቤተክርስቲያን እንጎበኛለን(ሉቃ1፡39-80)። የካህኑ የዘካሪያስና ኤልሳቤጥ ቤት፣ የማሪያምንም ምንጭ እንመለከታለን። በፍጻሜውም መጥምቁ ዮሐንስ በይፋ አግልግሎት የጀመረበትን ምድረበዳ እንጎበኝና የራት ጊዜና አዳራችን በኢየሩሳሌም ይሆናል።
ይህ ዕለት የግል ጉዳያችሁንና አንዳንድ ግብይት የምታከናውኑበት ቀን ይሆንና ማምሻውን ወደ ሀገራችሁ በረራ ለማድረግ ወደ ኤርፖርት የምትሸኙበት ጊዜ ይሆናል።
