logo

Overview

Easter 2026 - በኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና ቅድስት አርሴማ ገዳም በካሊፎርኒያ የተዘጋጀ
Jerusalem, Israel
Duration: 11 days
AJET Israel image
AJET Israel
$1,980

About your trip


Easter 2026 Tour to Jerusalem


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያን በዳግማዊቷ ዋልድባ ገዳም በካሊፎርኒያ የተዘጋጀ የፋሲካ የበረከት ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም።


በአይነቱ ልዩ የሆነ የኢየሩሳሌም ጉዞ ለፋሲካ የተዘጋጀ። ይህ ጉዞ በራሳችን ገዳም የትም ቦታ በማያገኙት ዋጋ የቀረበ ከመሆኑም በላይ በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ለገዳማችን የበኩልዎን ያደርጋሉ። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ማለት ነው።  


ይህ የበረከት ጉዞ በብፁዕ ዶ/ር አቡነ ቴዎፍሎስ የሚመራ ይሆናል። 


Easter 2026 Pilgrimage to Jerusalem

Join us on a once-in-a-lifetime spiritual journey to Jerusalem, organized by St. John the Baptist & St. Arsema Ethiopian Orthodox Tewahedo Monastery in California.


Experience Easter in the Holy Land at an unbeatable price, while also supporting our monastery. This is more than just a trip—it’s an opportunity to deepen your faith and contribute to a meaningful cause.


The journey will be led by His Excellency Dr. Abune Teofilos.


Don’t miss this blessing-filled pilgrimage!

ስለ ምዝገባና ክፍያ

ማሳሰቢያ፡

ከየትኛውም የዓለም ክፍል ቢነሱ የተጠቀሱት የፓኬጅ ዋጋ አንድ አይነት ነው። የበረራ ትኬት ዋጋ ብቻ እንደሚነሱበት ከተማ ሊለያይ ይችላል።


💳 የክሬዲት ካርድ ተጨማሪ ክፍያን ለማስወገድ ከስር በተጠቀሰው የባንክ አካውንት በማስተላልፍ ክፍያ ማድረግ ይችላሉ። ይህም  በአማካይ እስከ $130 የክሬዲት ካርድ ክፍያን ያድንልዎታል ።


ያስተውሉ   ➤  የበረራ ትኬት ዋጋ በማንኛውም ሰዓት የሚቀያየር መሆኑን ከወዲሁ እንዲያውቁ እናሳስባለን። ስለዚህም ጉዞው በቀረበ ቁጥር ሊጨምር ስለሚችል በቶሎ ቦታዎትን ያስይዙ። 


✓  እንደምርጫዎ ከበረራ ትኬት ጋር ወይም ያለበረራ ትኬት በመክፈል መመዝገብ ይችላሉ።


✈️ የበረራ መነሻዎ ከተማ ከስር ከተጠቀሱት ከተማዎች ውጭ ከሆነ በስልክ ቁጥር  +1 (703)416-9494 ወይም +972 549  21 20 30 (whatsApp) ያነጋግሩንና ትኬትዎትን እናስተካክልልዎታለን። 


✈️  የበረራ ትኬት ከኛ ካልገዙ፤ እስራኤል የሚገቡበት ቀን ዕሮብ April 8, 2026 መሆኑን ያረጋግጡ። 


🏨  ሆቴል ክፍል ማግኘት የሚችሉት (Hotel Check-in) ዕሮብ ከቀኑ  9:00 (03:00 PM)ሰዓት ጀምሮ ነው።


📞 ማንኛውም የምዝገባ ችግር ካጋጠምዎት ሌላም ጥያቄ ካልዎት ከስር በተጠቀሱት የስልክ ቁጥር ያነጋግሩን። 


Bank Account Information


Name: PanAf Travel LLC

Bank: Navy Federal Credit Union

Account number: 7135692700

Routing number: 256074974

USA

Phone: +1 (703) 416-9494


ማንኛውም ጥያቄ ካልዎት

ለማንኛውም ተጨማሪ ጥያቄዎችና የምዝገባ ወይም የክፍያ ችግሮች ካጋጠምዎት በሚቀጥለው አድራሻ ያነጋግሩን፥


ካሊፎርኒያ : +1 (323) 206-2572

ለሰሜን አሜሪካ - +1 (703)416-9494

ለአውሮፓ - +972 549 21 20 30 (whatsApp)



What's included

ሆቴል -Hotel Accommodation

Double Occupancy

ቁርስ ምሳ እራት (ብፌ) - Meal

ምሳ ከፋሲካ ቀን ነው የሚጀምረው

የቅዱሳዊ ቦታዎች ጉብኝት

ጉብኝት በዘመናዊ አውቶቡስ

የዓርብ ስቅለትና ፋሲካ ቅዳሴ በጎልጎታ

Friday Sigdet and Easter Night in Golgota, Jerusalem

ከኤርፖርት ወደ ሆቴል ትራንስፖርት

በግሩፕ ለሚገቡ ብቻ - Airport Transfer, only if arrived with a group

የጉብኝት ቦታዎች የመግቢያ ክፍያ

Site Entrance Fee

አማርኛ ተናጋሪ አስጎብኚ

Experienced Amharic speaking Guide

What's not included

የበረራ ትኬት - Int. Flight

Contact us to secure the best price for your flight. ለጥሩ የበረራ የትኬት ዋጋ ያነጋግሩን።

ቲፕ - Gratitude

ለአስጎብኚ እና ለአውቶቡስ ሾፌር የሚሰጡ ቲፖች

ከአየር ማረፊያ የግል ትራንስፖርት

ከአየር ማረፊያ ትራንስፖርት በግላቸው ለሚመጡ

'የመንገደኛ ኢንሹራንስ

Insurance Coverage for Covid-19 -ኮቪድን የሚያጠቃልል

የቪዛ ክፍያ - Visa Fee ($25)

የእስራኤል የመግቢያ ቪዛ ለሚያስፈልጋቸው ብቻ ($25)

ከምግብ ጋር የሚወሰዱ ተጨማሪ መጠጦች

Day 1

Day 1 image

የጕዞ መነሻ

በዚህ ዕለት ጕዞ ወደ ቅድስት ሀገር የሚደረግበት ቀን ይሆንናል። 

Day 2

Day 2 image

ሰላምታና የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል

በዚህ ዕለት ቤንጎርዮን የእስራኤል አየር ማረፊያ ያርፋሉ፤ በዚያም  የአስጎብኚዎ  ድርጅት የሥራ ባልደረቦች ልባዊና መልካም የሆነ አቀባበል ያደርጉለዎታል። በቀጥታም ወደ ያዝንለዎት ሆቴል እንወስደዎትና የእረፍት ጊዜ ያደርጋሉ። ራትና  አዳራችን በተያዘልዎት ሆቴል  ይሆናል። የመንገዱን ድካምዎን  በምቹው የሆተል መኝታ አሳርፈው በማግስቱ  ኢየሱስ ክርስቶስ እግሮቹ በተመላለሱበት ምድር እርሰዎም ለመራመድ ይዘጋጃሉ።   

Day 3

Day 3 image

ጸሎተ ሐሙስ ፣ ዕፅበተ እግር


ከቍርስ በኋላ ቅዱስ ቦታ በሆነው በደብረ ጽዮን (2ሳሙ15፣30 ማር 11፣1 ሐዋ 1፣12) ጕብኝታችንን እንጀምራለን። በመቀጠል ጌታ የደቀ መዛሙርቱን እግር ወዳጠበበትና ከነርሱም ጋር የመጨረሻዋን የፋሲካን ራት ወደበሉበት ደርብ/ቤት እናቀናለን(ዮሐ13፡4)፤ ከዚያም ወደ ንጉሥ ዳዊት የመቃብር ሥፍራና ቅድስት ድንግል ማርያም ወዳረፈችበት ወደ ዶርሚሽን ቤተክርስቲያን እንቀጥላለን። በጽዮን በር በኩል ወደ ጥንታዊቷ የኢየሩሳሌም ከተማ እንገባና የአይሁድ ብቸኛ ቅዱስ ቦታ፣ ለሙስሊሞች ደግሞ ሦስተኛው ቅዱስ ቦታ የሆነውን ምዕራባዊውን የቤተ መቅደስ ክፍል እንጎበኛለን፤ ከዚህ ሁሉ በኋላ የጸሎተ ሐሙስ ሥርዐትን ለመካፈል ወደ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንሄዳለን። ራትና አዳራችን በኢየሩሳሌም ይሆናል።

Day 4

Day 4 image

አርብ ስቅለት (ፍኖተ- መስቀሉ)

በዚህ ዕለት ኢየሱስ ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ ባልጋ ቍራኛ ተይዞ የነበረውን ሰው የፈወሰባትንና የመጠመቂያ ሥፍራ የነበረባትን ቤተ ሳይዳን/ቤተ ስዳ/ በመጎብኝት እንጀምራለን (ዮሐ 5፣ 2-9)። ከዚያም ቪያ ዶሎሮሳ የተባለውንና ኢየሱስ ካባድና ፅኑ ጸዋትወ መከራ ያለፈበትን ባለ 14 ጣቢያ መንገድ ከጲላጦስ የፍርድ አዳራሽ እንጀምርና ዳር'ዔል ሡልጣን ላይ ጕዞአችንን እናብቃለን። የአርብ ስቅለት ሥርዐትን እንካፈልና ራትና ኣዳራችን በኢየሩሳሌም ይሆናል።

Day 5

Day 5 image

ደብረ ዘይት ተራራ፣ የበዓለ ትንሣኤ ዋዜማ

በዚህ ዕለት ማለዳ ኢየሱስ በተሰቀለበት ቦታ በጎልጎታ የሚካሄደውን ሥርዐተ ቅዳሴን እንሳተፋለን። ከቍርስ በኋላ፣ በቀጥታ በመኪና ወደ ደብረ ዘይት ተራራ እንጓዛለን። እዚያ እንደደረስንም አስቀድመን ኢየሱስ ያረገበትን ሥፍራ - የዕርገት ቤተክርስቲያንን እንጎበኛለን። በመቀጠልም በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ለመግባት ወደ ጀመረባት ቦታ ወደ ቤተ ፋጌ እንሄዳለን(ሉቃ 19፣ 28-40)። ከዚያም ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ "አባታችን ሆይ" የሚለውን ጸሎት ያስተማረበትን ቦታ ፓተር ኖስተር ቤተክርስቲያን (ኢልዮና)ን እንጎበኛለን። ደብረ ዘይት ተራራ አናት ላይ ሆነን ከርቀት የጥንታዊቷን የኢየሩሳሌም ውብ መልክዐ-ምድራዊ ገጽታን እየተመለከትንም ደስ እንሰኛለን፣ ከደብረ ዘይት ተራራ ቍልቍል እንወርድና ጌታ ኢይሩሳሌምን ዐይቶ ወዳለቀሰላት(ሉቃ 19፡ 41-44) ወደ ዶሚንዮስ ፍለቨት የጸሎት ቦታ እናመራለን። ኢየሱስ ሲጸልይ ወደ ተያዘባት ወደ ጌቴሴማኒ ያትክልት ስፍራ(ማቴ 26፣ 36-58/ ሉቃ 26፡ 36-58) ወደ ታዋቂው የሕዝቦች ሁሉ ቤተክርስቲያን ጉዞኣችን እንቀጥላለን። የዕለቱ ጉዞአችን የቅድስት ድንግል ማርያምን መካነ መቃብር በመመልከት ያበቃል። ከምሳ በኋላ በሆቴላችን እረፍት የምናደርግበት ጊዜ ይኖረናል። አመሻሹ ላይ ሻማ የማብራት ሥነ-ሥርዐትና የትንሣኤ የዋዜማ ምሽት ወደ ሚካሄድበት ወደ ዳር'ዔል ሡልጣን እንሄዳለን። ሌሊት ወደ 9፡00 ሰዓት ገደማ ወደ ማረፊያ ሆቴላችን እንመለሳለን።

Day 6

Day 6 image

ዕለተ ሰንበት- የትንሣኤ ክብረ በዓል

በዚህች ዕለት የትንሣኤ ክብረ በዓል በሐሴት፣ በደስታ ብሎም ግሩም ከሆነ የፋሲካ ምሳ ጋር እናሳልፋለን። ኣዳር በኢየሩሳሌም ከተማ ይሆናል።

Day 7

Day 7 image

ኢያሪኮ፣ የዮርዳኖስ ወንዝና የጨው ባሕር

ቀኑን አስገራሚ መልክዐ-ምድራዊ አቀማመጥና ገጽታ ያለውን የይሁዳ ምድረ በዳን እየተመለከትን ዜኬዎስ የወጣበትን የሾላ ዛፍና የኤልያስን ምንጭ ወደ ምንመለከትበት ወደ ኢያሪኮ በመጓዝ እንጀምራለን። ኢየሱስ በሰይጣን ወደ ተፈተነበት ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ እንወጣለን። ከዚያም ኢየሰስ በዮሐንስ እጅ የተጠመቀበትን ልዩ የዮርዳኖስ ወንዝ ቦታ፣ ካሰር አል-ያሁድ እንጎበኛል። በደቡባዊው የሙት ባሕር ዳርቻ ወደ ምትገኘው፣ በዓለምም ካባሕር ጠለል በታች 400 ሜትር የመጨረሻው ረባዳ ቦታ ወደ ሆነው ወደ ዔይን ቦኬክ እንጓዛለን። በዚያም ደረጃውን በጠበቀ ባለ4 ኮከብ ሆቴል ውስጥ በዓለም እጅጉን በታወቀውና በጨው ማዕድን በበለጸገው ውሃ ወስጥ እንዝናናለን። ስፓ፣ ጃኩዚ፣ የመዋኛ ገንዳና በዚያ በሚገኙት የመዝናኛ አገልግሎት መስጫዎች ሆሉ እየተዝናናን ደስ እንሰኛለን።

Day 8

Day 8 image

ደበረ ታቦር፣ ቃና ዘገሊላ፣ ናዝሬት

የዕለቱን ጕዟችንን በታችኛው የገሊላ ክፍል በኩል በማድረግ የኢይዝራዔልን ሸለቆንና ብሎም እንደ ዮሐንስ ራዕይ መሠረት የሰውልጆች የመጨረሻው ጦርነት የሚደረግበትን የሚግዶን አስደሳች መልክዐ-ምድራዊ ገጽታን እየተመለከትንና ደስ እየተሰኘን በቀጥታ ጌታ ብርሃነ-መለኮቱን ወደ ገልጠበት ወደ ደብረ ታቦር እናመራለን። ኢየሱስ በሰረግ ቤት ታድሞ የወይን ጠጅ ባለቀባቸው ጊዜ የመጀመሪያውን ተአምራት ያደረገበትን(ዮሐ 2፡1-11)ቃና-ዘገሊላንና በዚያም የሚገኘውን ቤተክርስቲያን እንጎበኛለን። በመቀጠልም ወደ ናዝሬት በማምራት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ደስ ይበልሽ በማለት የኢየሱስን መወለድ ለድንግል ማርያምን ያበሠረበትን(ሉቃ 1፡26-38) ጥንታዊውን የብሥራት ዋሻን እንጎበኛለን። የዮሴፍን ቤትን እንመለከትና ወደ ማሪያም ምንጭ እንሄዳለን። አዳር በጥብርያዶስ ይሆናል።

Day 9

Day 9 image

የገሊላ ባህርንና አካባቢው

ከቍርስ በኋላ ጉዞአችንን ወደ ስብከቱ ተራራ እናደርጋለን። ከዚያም  ጌታችን የተራራውን ስብከት (አንቀጸ ብጹዓን) የሰበከበትን ተራራ እንጎበኛለን(ማቴ 5፡7)። በመቀጠልም ኢየሱስ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሳ አበርክቶ ለሕዝቡ ወደ መገበበት ቦታ(ማቴ 14፡14-43) ወደ ታብጋ እንሄድና የ4ኛው ክ/ዘመን የሞዛይክ ጣራ ያለውን ቸርች ኦፍ መልቲፕልኬሽን /የበርክቶ ቤተክርስቲያን/ን እንጎበኛለን። በመቀጠልም ናዝሬትን ትቶ በመምጣት መኖሪያው ያደረገባትንና በምድር ላይም አገልግሎቱን ወደ ጀመረባት በዘልማድም የኢየሱስ ከተማ እየተባለች ወደ ምትጠራው ወደ ቅፍርናሆም እናልፋለን። በዚያም በሁለተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ምኲራብንና የቅዱስ ጴጥሮስ መኖሪያ የነበረውን ቤት እንጎበኛለን። በምሳ ሰዓት ግሩም የሆነውን የቅዱስ ጴጥሮስን ዓሣ እንመገብና በጀልባ ላይ ተሳፍርን ኢየሱስ በእግሩ የተራመደበትን የገሊላን ባሕርን እንሻገራለን(ማቴ14፡22-23)። በዘመነ ኢየሱስ የነበረውን የዓሣ አጥማጅ ጀልባ፣ "የኢየሱስ ጀልባን በኪቡጽ ጊኖሣር እንጎበኛለን። ለራትና ለአዳር ወደ ሆቴላችን እንመለሳለን።

Day 10

Day 10 image

የኤልያስ ባዕት(ዋሻ)፣ ሐይፋ፣ ሎድ ፣ ቤተ ልሔም፣ ኢን ኬሬም

በዚህ ዕለት የቀርሜሎስ ተራራ የእግዚአብሔር የወይን ተክልንና የታላቁ ነቢይ የኤልያስን ባዕት/ዋሻ በመጎብኘት እንጀምራለን። ከዚያም በሐይፋ የሚገኝውንና ከፍ ካለው መልክዐ-ምድራዊ ገጽታ ላይ የተንጣለለውን፣ ባትክልትም የተዋበውን የባሂኢን ያምልኮ ሥፍራ ተመልክተን ወደ ቴል አቪቭ በሚወስደው በሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ መንገድ ኣድርገን ወደ ጃፋ እናመራለን። በዚያም ነቢዩ ዮናስ ከእግዚአብሔርና ከትእዛዙ ለመኮብለል መርከብ የተሳፈረበትን ቦታና(ዮና 1፡3) ብሎም ደግሞ ሐዋሪያው ቅዱስ ጴጥሮስ በስድስት ሰዓት ያህል ይጸልይ ዘንድ ወደ ጣራው የወጣበትን የቍርበት ፋቂው የስምዖን ቤት(ሐዋ 10፡9-19) ፣ጥንታዊቷንም የጃፋን ወደብ እንጎበኛለን።  በመቀጠልም  ከምሳ በሗላ ጉዞአችንን ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ቤተልሔም ይሆንና፣ በባሲልካ ኔቲቪቲ ምልክት የተደረገበትን የኢየሱስን የልደት ቦታ እንጎበኛለን(ሉቃ 2፣ 1-7)። መልአከ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ብሎ ለእረኞች የጌታን ልደት ያበሠረበትን፣ መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩበትን ሥፍራ(የወተት ዋሻ)ን እንመለከታለን( ሉቃ2፡8-18)። ከሰዓት በኋላ የመጥምቁ ዮሐንስን የልደት ቦታ ዔይን ካሬምን እንጎብኛለን። ማርያም ዘመዷን ኤልሳቤጥን ለመጎብኝት የሄደችበት ሀገርና ከእርሷም ጋር የተገናኘበትን ሥፍራ ላይ ያልውን ቤተክርስቲያን እንጎበኛለን(ሉቃ1፡39-80)። የካህኑ የዘካሪያስና ኤልሳቤጥ ቤት፣ የማሪያምንም ምንጭ እንመለከታለን። በፍጻሜውም መጥምቁ ዮሐንስ በይፋ አግልግሎት የጀመረበትን ምድረበዳ እንጎበኝና የራት ጊዜና አዳራችን በኢየሩሳሌም ይሆናል።

Day 11

Day 11 image

ነጻ የግብይትና ወደ ሀገራችሁ መመለሻ ቀን

ይህ ዕለት የግል ጉዳያችሁንና አንዳንድ ግብይት የምታከናውኑበት ቀን ይሆንና ማምሻውን ወደ ሀገራችሁ በረራ ለማድረግ ወደ ኤርፖርት የምትሸኙበት ጊዜ ይሆናል።

Location

Loading Map…

1. Jerusalem, Israel

Jerusalem, Israel

About your organizer

AI
AJET Israel
AJET Israel and Africa–Israel Business Networking is connecting people through meaningful travel, conferences, and business engagement. We specialize in curated tours, B2B travel solutions, and Business networking initiatives that build lasting partnerships.

Reviews

Photo gallery

Image 0
Image 1
Image 2
Image 3
© 2026 AJET Israel